ቋንቋ


English English
አማርኛ Amharic
العربية Arabic
العربية - الأردن Arabic (Jordanian)
العربية التونسية Arabic (Tunisian)
Armenian Armenian
Sign Language American Sign Language
বাংলা Bengali (India)
भोजपुरी Bhojpuri
Bosanski Bosnian
မြန်မာဘာသာ Burmese
中文(繁體,香港) Cantonese (Traditional)
中文(简体) Chinese (Simplified)
中文(繁體) Chinese (Traditional)
Hrvatski Croatian
Français French
Deutsch German
ગુજરાતી Gujarati
Hausa Hausa
हिन्दी Hindi
Bahasa Indonesia Indonesian
Italiano Italian
日本語 Japanese
ಕನ್ನಡ Kannada
한국어 Korean
Кыргызча Kyrgyz
کوردی Kurdish
ພາສາລາວ Lao
𑒧𑒻𑒟𑒱𑒪𑒲 Maithili
മലയാളം Malayalam
मराठी Marathi
नेपाली Nepali
ଓଡ଼ିଆ Odia
فارسی Persian/Farsi
Polski Polish
Português Portuguese
ਪੰਜਾਬੀ Punjabi
ਪੰਜਾਬੀ (ਪੱਛਮੀ) Punjabi (Western)
Русский Russian
Română Romanian
Slovenščina Slovenian
Soomaali Somali
Español Spanish
Kiswahili Swahili
தமிழ் Tamil
తెలుగు Telugu
ไทย Thai
Türkçe Turkish
اردو Urdu
Tiếng Việt Vietnamese
Yorùbá Yoruba

እግዚአብሔር ተራ ሰዎችን ይጠቀማል


ወደ ዙሜ ሥልጠና እንኳን በደህና መጣችሁ! ዙሜ(Zúme) የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “እርሾ” ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ እንዳለው የእግዚአብሔር መንግሥት ጥቂት “እርሾ” ወስዳ ብዙ ሊጥ ውስጥ የከተተችን ሴት ትመስላለች፡፡ ሴት የዋ እርሾውን በሊጡ ውስጥ ስታኖረውም፣ እርሾው ሊጡን ሁሉ እስኪያቦካው ድረስ ይስፋፋል፡፡ በዚህም ንግግሩ ኢየሱስ ያስረዳው አንድ ተራ ሰው በጣም ትንሽ ነገር ወስዶ ታላቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነን ነገር ለመፍጠር ሊጠቀምበት እንደሚችል ነው! ሕልማችን ኢየሱስ ያለውን ለማድረግ ነው… በዓለም ሁሉ ያሉ “ተራ” የሚባሉ ሰዎች ታናናሽ መሣሪያዎችን ወስደው በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ታላቅ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ መርዳት! ኢየሱስ ለተከታዮቹ በመጨረሻ ጊዜ የሰጣቸው ትዕዛዝ ለመረዳት ቀላል ነበሩ፡፡ እንዲህ ነው ያላቸው፡- “ሥልጣን ሁሉ በሰማይ እና በምድር ተሰጠኝ፡፡ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” የኢየሱስ ትዕዛዝ ቀላል ነው፤ “ደቀ መዛሙርት አድርጉ” የሚል ነው፡፡ ትዕዛዙን እንዴት እንደሚፈጽሙም የነገራቸው ነገር ቀላል ነው፤ በምትሄዱበት ሁሉ ደቀ መዛሙርትን አድርጉ፡- በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ያዘዘውን ሁሉ እንዲያከብሩ እነርሱን በማስተማር ደቀ መዛሙርት አድርጉ፤ ሆኖም አንድን ሰው ደቀ መዝሙር ማድረግ ምን ምን ደረጃዎች አሉት? 1 – ደቀ መዛሙርት ማድረግ ያለብን ሁልጊዜ ነው፤ የትም ብንሄድ፤ 2 – አንድ ሰው ኢየሱስን ለመከተል ሲወስን - መጠመቅ አለበት፡፡ 3 – አንድ ሰው ኢየሱስን በመከተል እያደገ ሲሄድ፣ ኢየሱስ ያዘዘውን ሁሉ እንዴት መታዘዝ እንዳለበት ማስተማር ይገባል፡፡ ኢየሱስ ካዘዛቸው ነገሮች አንዱ ደቀ መዝሙር ማድረግ እንደመሆኑ፣ ኢየሱስን የሚከተል ሁሉ ሰዎችን እንዴት ደቀ መዝሙር ማድረግ እንዳለበት መማር አለበት፡፡ ደቀ መዛሙርት ደቀ መዛሙርትን ማፍራት አለባቸው፡፡ እነዚያ ደቀ መዛሙርት የሆኑትም ደቀ መዛሙርትን ማፍራት አለባቸው፡፡ ደቀ መዛሙርትን ማብዛት አለባቸው፡፡ ዙሜ የሚሠራውም እንደዚህ ነው፡፡ ልክ እንደ እርሾ ነው፤ ሊጡ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ በሊጡ ውስጥ ይሠራል፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ደቀ መዛሙርትን እንዲፈሩ ሲያዛቸው፣ አንድ የተስፋ ቃል ሰጥቷቸዋል፤ “እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” ብሏቸዋል፡፡ የኢየሱስ ተከታይ ሁሉ ታዲያ እርሱ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር የመሆኑን ነገር ሊያስበው ይገባል፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ እንዳለው ከእኛ ጋር ስለሆነ! ይህም ማለት የእርሱ ተከታይ የሆንን እኛ እያንዳንዳችን ደቀ መዛሙርትን እንድናፈራ ለሚፈልገው ለኢየሱስ ራሳችንን ማስገዛት አለብን ማለት ነው፡፡ እርሱ ከእኛ የሚፈልገው ይህንን ነው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- “… ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ... ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤” እኛን የላከን ኢየሱስ የተደገፈበት ሥልጣን … የራሱ ሥልጣን ነው፡፡ እርሱ እንዳለውም ከዚህ የሚበልጥ ሥልጣን የለም፡፡ ከእርሱም የሚበልጥ ሥልጣን ያለው ትውፊት የለም፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ሥልጣን ያለው ባህልም የለም፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ሥልጣን ያለው ሕግም በምድር ላይ አልታየም፡፡ ኢየሱስ ያለው ይህንን ነው፡- “ሂዱና ደቀ መዛሙርት አድርጉ፡፡” ሥራው ሁሉ ተሠርቶ እስኪያልቅ ድረስ፣ ልክ እንደ ዙሜ - ልክ እንደ እርሾ - መሄዳችንን እና ማደጋችንን እንቀጥላለን፡፡